ፈረንሳይ ሞሮኮን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈች
ፈረንሳይ ሞሮኮን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፈች አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫው የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ፈረንሳይ ሞሮኮን 2 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። በቦስተን ጁሌት ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የፈረንሳይን ግቦች ኪሊያን ምባፔ እና ኦስማን ዴምቤሌ አስቆጥረዋል። በመጀመሪያው አጋማሽ ፍጹም ቅጣት ምት የሳተው ምባፔ በዚህ ዓለም ዋንጫ ከሊዮኔል ሜሲ እኩል 8 ግቦች በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን በጋራ እየመራ ይገኛል። ፈረንሳይ በሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ የፍጻሜ ተፋላሚ ለመሆን በግማሽ ፍጻሜው ከስፔን እና ቤልጂየም አሸናፊ ጋር ትገናኛለች፡፡
Read the full story at fanatelevision ↗