" ህጋዊው የውል ማሻሻያ ለ2 ዓመታት ይቆያል " - ቢሮው
" ህጋዊው የውል ማሻሻያ ለ2 ዓመታት ይቆያል " - ቢሮው በአዲስ አበባ የ2019 በጀት ዓመት የቤት ኪራይ ዓመታዊ የጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ ሆኖ እንዲጸድቅ መደረጉ ይታወሳል። ከዚህ ተመን በላይ መጨመር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊው የውል ማሻሻያም ለ2 ዓመታት ይቆያል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አሳውቋል። ከህጋዊ አሰራር ውጪ የሚደረጉ "የመንደር ውሎች" የተከለከሉ ሲሆን ውል በማያድሱና ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ ቅጣት ይጣላል። የውል እድሳት ጊዜያቸው አልፎ አከራይም ተከራይም አብረው ኖረው እድሳት ሳይፈጽሙ እስከ 2 ወር ከቆዩ የ1 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይጣልባቸዋል። ውል ሳያድሱ 3 ወር እና ከዚያ በላይ የቆዩ የ2 ወር የቤት ኪራይ ቅጣት ይከፍላሉ። አዲስ ተከራይ አስገብተው ውል ያላደሱ እና ያላስመዘገቡ የ1 ወር የቤት ኪራይ ይቀጣሉ።…
Read the full story at tikvahethiopia ↗