ያለ ብቃት ማረጋገጫ ዲግሪ የያዙ ተመራቂዎች የብቃት ፈተና ሊሰጣቸው ነው‼

WASULIFEneutral2026-07-10 15:42:19 UTC
AdYour ad here[email protected]

ያለ ብቃት ማረጋገጫ ዲግሪ የያዙ ተመራቂዎች የብቃት ፈተና ሊሰጣቸው ነው‼ ​ከመስከረም 2010 እስከ 2015 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ከቀድሞ ዲፕሎማ (12+2)፣ ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ስልጠና በኋላ፣ የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ገብተው ለተመረቁ ዜጎች የብቃት ፈተና ሊሰጥ መሆኑ ተገለጠ። ​የኢፌዴሪ ትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን ባዘጋጀው የማሻሻያ መመሪያ ረቂቅ መሠረት፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MA) እና ሦስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙ ባለሙያዎች፣ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መሥፈርት መሠረት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ ብቻ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል። ​ባለሥልጣኑ በመመሪያው ማሻሻያ ላይ ከባለድርሻ አካላት አስተያየት እየሰበሰበ ይገኛል።…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]