ወደ ሚዛን አማን የቅደመ ምረቃ በረራ ጀመረ
ወደ ሚዛን አማን የቅደመ ምረቃ በረራ ጀመረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የሚያደርገውን የቅደመ ምረቃ በረራ በዛሬው ዕለት ጀምሯል። አየር መንገዱ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሦስት ቀናት በረራ የሚያደርግ ሲሆን÷ ይህም ለማሕበረሰቡ ፈጣን፣ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ ያስችላል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ኤርፖርቶች ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጌታነህ አደራ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ ፍቅሬ አማን እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ ሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗