መረጃ‼️

ADDIS_NEWSneutral2026-07-11 05:16:30 UTC
AdYour ad here[email protected]

መረጃ‼️ አብዛኛው አክሲዮኑ ለግል ባለሃብቶች የተሸጠው የፓኪስታን አየር መንገድ፣ የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ወልደ ማርያምን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አድርጎ ለመቅጠር ማሠቡን ብሉምበርግ ዘገበ። አየር መንገዱ በመጪው እሁድ የተወልደን ሹመት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች እንደነገሩት የዜና ምንጩ ጠቅሷል። የፓኪስታን አየር መንገድ "በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት" እና "በእዳ" ምክንያት ለከፍተኛ ኪሳራ ከተዳረገ በኋላ ለዓመታት በመንግሥት ሲደጎም የቆየ አየር መንገድ ነው። ኾኖም ካለፈው ሚያዝያ ወዲህ ባለሃብቶች የአየር መንገዱን 75 በመቶ አክሲዮን የገዙት ሲኾን፣ ቀሪውን 25 በመቶ ከመንግሥት ለመግዛት እያሰቡ መሆኑን ዘገባው አመልክቷል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]