ሆቴሎች መኝታ ላይ የ5% ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ተጣለ‼

WASULIFEneutral2026-07-11 08:37:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሆቴሎች መኝታ ላይ የ5% ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ተጣለ‼ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማዋን ገቢና መሠረተ ልማት ለማሳደግ “የመኝታ አገልግሎት ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ደንብ ቁጥር 204/2018” አወጣ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፈረሙትና ከሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የጸናው ይህ ሕግ፣ ከ1 እስከ 7 ኮከብ ሆቴሎችን፣ ሪዞርቶችን፣ የእንግዳ ማረፊያዎችንና ፔንሲዮኖችን ያጠቃልላል። 📌 ማንኛውም ተጠቃሚ ከክፍል ዋጋው ላይ (VAT ሳይጨምር) 5% ማዘጋጃ ቤታዊ ታክስ ይከፍላል። 📌 ተቋማት የክፍል ብዛትና ዋጋ በገቢዎች ቢሮ መመዝገብ፣ በደረሰኝ ላይ ታክሱን በግልጽ ማሳየት አለባቸው። 📌 ደረጃ "ሀ" በየወሩ፣ ደረጃ "ለ" በየሦስት ወሩ የሰበሰቡትን ገቢ ሪፖርት አድርገው በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። 📌 ታክሱን መክፈል ከንግድ ፈቃድ ዕድሳት ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ ሪፖርት…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]