ጋምቤላ ከ7 ቶን በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገባ!

ADDIS_NEWSneutral2026-07-11 08:58:59 UTC
AdYour ad here[email protected]

ጋምቤላ ከ7 ቶን በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገባ! የጋምቤላ ክልል ማዕድን ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ከ7 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የወርቅ ምርት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን አስታውቋል። ኤጀንሲው ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው፥ ይህ ታላቅ ስኬት የተመዘገበው በክልሉ ያለውን እምቅ የወርቅ ማዕድን ሀብት በሚገባ ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ነው። የወርቅ ምርቱ የተሰበሰበው በክልሉ በሚንቀሳቀሱ ባህላዊ፣ ልዩ አነስተኛ እና የወርቅ አምራች ኩባንያዎች አማካኝነት መሆኑም ተገልጿል። ይህንን ከፍተኛ የሀብት ክምችት ገቢ ለማድረግ የማዕድን ሀብት ልማት አሰራርን በማዘመን ዘርፉን ከብክነት ለመታደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል። በተለይም በማዕድን ዘርፉ ውስጥ የሚስተዋለውን ሕገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ለመከላከል…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]