" ሁኔታው አሳዛኝ ነው። ትናንትና ታጣቂዎችን ኢላማ ያደረገ ሌላ የድሮን ጥቃት ነበር እርሱ አላስገረመንም ፤ የዛሬው ግን ሰላማዊ ሰዎችን የመታ ነበር " - የራማ ነዋሪ
" ሁኔታው አሳዛኝ ነው። ትናንትና ታጣቂዎችን ኢላማ ያደረገ ሌላ የድሮን ጥቃት ነበር እርሱ አላስገረመንም ፤ የዛሬው ግን ሰላማዊ ሰዎችን የመታ ነበር " - የራማ ነዋሪ ትግራይ ክልል ራማ ከተማ በደረሰ የድሮን ጥቃት ቢያንስ 11 ሰዎች መገደላቸውን የፈረንሳይ ዜና ወኪል (ኤኤፍፒ) የህክምና ምንጮችን እና የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ ዘግቧል። እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ገለፃ፣ የመጀመሪያው ጥቃት ሐሙስ ምሽት 3:00 አካባቢ ማሽላ የጫነች የግል የጭነት ተሽከርካሪ ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ በነገታው አርብ ማለዳ ደግሞ በተመታችው ተሽከርካሪ ዙሪያ የተበተነውን እህል ሰዎች እየሰበሰቡ እያለ ሁለተኛ የድሮን ጥቃት ተከስቷል። በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 13 መሆኑን አንድ የዓይን እማኝ ሲናገሩ፣ በአቅራቢያ የሚገኝ የሆስፒታል የህክምና ምንጭ በበኩሉ የ11 ሰዎችን ህልፈት ማረጋገጡን እና ተጨማሪ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗