አላማጣ - መረዋ መስመር የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ‼
አላማጣ - መረዋ መስመር የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ‼ በራያ አላማጣ ወረዳ መረዋ መስመር «ዓዲ ደረባ» በተባለ አካባቢ አንድ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ በመገልበጡ የ4 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ከገበያ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ ሰዎችን አግዟት በነበረችው በዚህ አውቶቡስ ላይ በደረሰው አደጋ በ39 ሰዎች ላይ ከባድና ቀሊል የአካል ጉዳት ደርሷል። ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በአላማጣ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑ ታውቋል። ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr…
Read the full story at wasulife ↗