እንግሊዝ ለግማሽ ፍፃሜው ደረሰች

EBCNEWSNOWneutral2026-07-12 00:21:14 UTC
AdYour ad here[email protected]

እንግሊዝ ለግማሽ ፍፃሜው ደረሰች ******************* በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ እንግሊዝ ኖርዌይን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜው ደርሳለች። ከሌሊቱ 6 ሰዓት የተጀመረው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በመደበኛው ሰዓት (በ90 ደቂቃ) 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ነው የተጠናቀቀው። አንድሪያስ ሼልድረፕ ኖርዌይን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ በ36ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን 45+2 ደቂቃ ላይ አቻ አድርጓል። መደበኛ ሰዓቱ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ያመሩ ሲሆን ጁድ ቤሊንግሃም እንግሊዝን አሸናፊ ያደረገችውን ግብ 93ኛ ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል። ጁድ ቤሊንግሃም በዓለም ዋንጫው እስካሁን ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን ሲያስቆጥር አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። #EBC #EBCSPORT…

Read the full story at ebcnewsnow ↗
AdYour ad here[email protected]