የፍቅር ተአምር፦ የእግር ጣቱ በሚስቱ በመነከሱ ከ7 ዓመት በኋላ ከኮማ የነቃው ባል

ADDIS_NEWSneutral2026-07-12 09:19:06 UTC
AdYour ad here[email protected]

የፍቅር ተአምር፦ የእግር ጣቱ በሚስቱ በመነከሱ ከ7 ዓመት በኋላ ከኮማ የነቃው ባል ​በቻይና የሚኖሩት ሶንግ ሜይ የተባሉ ሚስት፣ ለሰባት ዓመታት ያህል በኮማ (vegetative state) ውስጥ የነበረውን ባለቤታቸውን ዣኦ ጂንቂያንን ባልተለመደ መንገድ ከሞት አፋፍ መልሰውታል። ባልየው በፈረንጆቹ 2019 የሶስት ዓመት ህጻን ለማዳን ሲሞክር ከ6 ሜትር ከፍታ ላይ ወድቆ ከባድ የአንጎል ጉዳት ደርሶበት ነበር። ​ዶክተሮች የነርቭ መነቃቃት ለመፍጠር የእጅና እግር ጣቶቹን እንዲያነቃቁ በሰጧት ምክር መነሻነት፣ ሚስትየው በድንገት የባለቤቷን የእግር ጣት ስትነክሰው በሰውነቱ ላይ መጠነኛ ምላሽ አስተውላለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ለዓመታት የባለቤቷን እግር በላስቲክ እየጠቀለለች የመንከስ ተግባሯን ቀጠለች። ​ይህ ያላሰለሰ ጥረት ፍሬ አፍርቶ ባልየው ሰኔ 30 ቀን ዓይኑን ገልጦ ነቅቷል።…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]