በአዲስ አበባ የግንባታ ግብዓቶች አመራረት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተጣለ

ADDIS_NEWSneutral2026-07-12 12:20:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

በአዲስ አበባ የግንባታ ግብዓቶች አመራረት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ተጣለ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በከተማዋ ውስጥ የሚከናወኑ እንደ አሸዋ፣ ድንጋይ፣ ጠጠር እና ቀይ አፈር ያሉ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች አመራረትን የሚደነግግ አዲስ መመሪያ አውጥቷል። በዚህም መሠረት ማምረት የሚፈልጉ አካላት በገለልተኛ አካል የተጠና የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማቅረብ፣ ለባለሥልጣኑ የዋስትና ገንዘብ ማስያዝና ሕጋዊ ፍቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል። የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ያላቸው ባለይዞታዎች ያለ ፍቃድ ማምረት ቢችሉም፣ የተመረተውን ግብዓት ግን ከራሳቸው ፍጆታ ውጭ ለሽያጭ ማቅረብ በጥብቅ ተከልክሏል። ደንቡ የአካባቢን ደኅንነትና ማኅበራዊ መረጋጋትን ለመጠበቅ ሲባል በማምረቻ ቦታዎች ላይ ጥብቅ ገደቦችን አስቀምጧል። በዚህም መሠረት በሃይማኖትና ቀብር ቦታዎች፣ ታሪካዊ ቅርሶች…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]