የቤት ኪራይ አልቀመስ ብሏል‼️

ADDIS_NEWSneutral2026-07-13 08:55:45 UTC
AdYour ad here[email protected]

የቤት ኪራይ አልቀመስ ብሏል‼️ በአዲስ አበባ ከተማ እያጋጠመ ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ መናር ከነዋሪዎች የመክፈል አቅም በላይ እየሆነና ጣሪያ እየነካ መምጣቱ ተሰምቷል። በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እያሻቀበ የሚገኝ ሲሆን፣ ለአንድ መደበኛ ክፍል ቤት ከ25 ሺህ እስከ 30 ሺህ የኢትዮጵያ ብር እየተጠየቀ ይገኛል። ባለ ሁለት እና ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ደግሞ ዋጋቸው በአስገራሚ ሁኔታ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ለነዋሪዎች ለመጥራት እንኳ የሚያስፈራ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነግሯል። ይህ የቤት ኪራይ ዋጋ በዚህ ፍጥነት ሊያሽቀበቅብ የቻለባቸው ዋነኛ ምክንያቶች በሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች በጸጥታና አለመረጋጋት ምክንያት ደኅንነት ፍለጋ ወደ ዋና ከተማዋ አዲስ አበባ የሚደረገው ፍልሰት በከተማዋ ያለውን የቤት ፍላጎት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]