የነዳጅ ዋጋ 4 በመቶ ጨመረ
የነዳጅ ዋጋ 4 በመቶ ጨመረ የአሜሪካ እና ኢራን ግጭት ማገርሸቱን ተከትሎ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል። በዓለማቀፍ ደረጃ 3.9% በመጨመር 78.96 ዶላር የገባ ሲሆን በአሜሪካ የነዳጅ ገበያው 4% በመጨመር 74.26 ዶላር መግባቱ ተገልጿል። ሁለቱ ሀገራት ግጭቱን ለማቆም እና የሆርሙዝ ሰርጥን በመክፈት የንግድ መርከቦች እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተደረገው ስምምነት እክል ገጥሞታል። በትናንትናው እለት አሜሪካ በኢራን የነዳጅ ማደያዎች ላይ ጥቃት ያደረሰች ሲሆን፣ ኢራንም በሰርጡ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች። በተጨማሪ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በጎረቤት ሀገራት ኩዌት፣ ባህሬን እና ጆርዳን ላይ የአሜሪካን ወታደራዊ ስፍራ ኢላማ ያደረገ ጥቃት ፈጽሟል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗