ከ69 ሚሊዮን ብር በላይ ከደንብና መመሪያ ውጪ ወጪ መደረጉ ተገለጸ‼️
ከ69 ሚሊዮን ብር በላይ ከደንብና መመሪያ ውጪ ወጪ መደረጉ ተገለጸ‼️ ደንብና መመሪያን ሳይከተሉ ክፍያን የፈጸሙ 89 ተቋማት በኦዲት ግኝት መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አስታውቀዋል። የተከፈሉ ክፍያዎች በተቀመጠው መመሪያ መሠረት መከፈላቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ የኦዲት ምርመራ፣ 89ኙ ተቋማት ደንብና መመሪያ ሳይከተሉ ደሞዝ፣ የውሎ አበል፣ ጥቅማጥቅምና የመሳሰሉ ክፍያዎችን ከደንብ ውጪ መፈጸማቸው እንደተረጋገጠ፤ በዚህም 69 ሚሊዮን 3 መቶ 66 ሺህ 985 ብር መገኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር አቶ አመንቴ መቻሉ ተናግረዋል። ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ 22 ሚሊዮን 1 መቶ 4 ሺህ 908 ብር፣ ኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ 5 ሚሊዮን 21 ሺህ 528 ብር እና ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗