ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብን ሙሉ ለሙሉ አነሳ!
ብሔራዊ ባንክ የብድር ገደብን ሙሉ ለሙሉ አነሳ! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በባንኮች ላይ ጥሎት የነበረውን ጊዜያዊ የብድር ገደብ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ። ባንኩ ይህንን የወሰነው ወደ ገበያ መር የገንዘብ ፖሊሲ ሥርዓት ለመሸጋገር ያስቀመጠው ግብ በመሳካቱ እንደሆነ ገልጿል። ይሁን እንጂ የብድር ገደቡ መነሳት የገንዘብ ፖሊሲው መላላኩን እንደማያሳይ የገለጸው ባንኩ፣ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የፖሊሲ ወለድ ምጣኔውን በአንድ በመቶ እንዲጨምር አድርጓል። በተጨማሪም ባንኮች ከልክ ያለፈ ብድር እንዳይሰጡ የሚቆጣጠር አዲስ የጥበቃ ማዕቀፍ አስተዋውቋል። በሌላ በኩል የወጪ ንግድ ወጪን ለመቀነስና ላኪዎችን ለማበረታታት፣ የውጭ ምንዛሬ ኮሚሽን ምጣኔ ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል። የወጪ ንግድ ገቢን ለባንክ የማስረከብ ግዴታም ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ…
Read the full story at addis_news ↗