የባንኮች የማበደር ገደብ ተነሳ‼
የባንኮች የማበደር ገደብ ተነሳ‼ የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ (ቁጥር 7) ስብሰባ ዋና ዋና ውሳኔዎችና የኢኮኖሚ አፈጻጸም አጭር መግለጫ:- ፩. ዋና ዋና የፖሊሲ ውሳኔዎች 📌የብድር ገደብ መነሳት፦ በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የዓመታዊ የብድር ዕድገት ገደብ (Credit Cap) ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ተወስኗል። 📌 የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ፦ የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ወለድ ምጣኔ (Policy Rate) በ1.0 በመቶ ነጥብ ከፍ በማለት ከ15 በመቶ ወደ 16 በመቶ እንዲያድግ ተደርጓል። 📌 የውጭ ምንዛሬ ተመላሽ ግዴታ (FX Surrender)፦ ላኪዎችና የውጭ ምንዛሬ አስገኚዎች ለባንኮች ገቢ የሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ ግዴታ ከ50 በመቶ ወደ 30 በመቶ ዝቅ እንዲል ተወስኗል። 📌 የኮሚሽን ምጣኔ ቅነሳ፦ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ግዢ ጋር ተያይዞ የሚያስከፍሉት የኮሚሽን ምጣኔ ከ2.5…
Read the full story at addis_reporter ↗