የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን፣ ሁሉም የበይነ መረብ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ሊያስገድድ መኾኑን አስታወቀ።

ADDIS_NEWSneutral2026-07-14 04:58:49 UTC
AdYour ad here[email protected]

የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን፣ ሁሉም የበይነ መረብ ጣቢያዎች እንዲመዘገቡ ሊያስገድድ መኾኑን አስታወቀ። ባለስልጣኑ፣ የበይነ መረብ ጣቢያዎች ተመዝግበው ብቻ እንዲሠሩ ለማስቻል የመገናኛ ብዙኀን ዋጁን ለማሻሻል ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጧል። አዋጁ፣ የበይነ መረብ ጣቢያዎች ምዝገባ በፈቃደኝነት ላይ ብቻ እንዲኾን የሚፈቅድ ነው። በዚህ ምክንያት፣ ፌስቡክን፣ ቲክቶክን እና ዩትዩብን በመሳሰሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘቶችን የሚያስተላልፉ አብዛኞቹ ድርጅቶችና ግለሰቦች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሳይወስዱና እውቅናና ፈቃድ ሳያገኙ እየሠሩ እንደሚገኙ ባለሥልጣኑ ጠቅሷል። @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]