በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያገረሸው ጦርነት በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ።
በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያገረሸው ጦርነት በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ። በእስያ ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን አንድ ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ1.9 በመቶ አሻቅቦ በበርሜል 84.87 ዶላር ደርሷል። በአሜሪካ ገበያ ደግሞ በ2 በመቶ ጨምሮ በበርሜል 79.75 ዶላር እየተሸጠ ነው። ግጭቱ ተባብሶ በመቀጠሉ ሰኞ ዕለት የብሬንት ነዳጅ ዋጋ በ3 በመቶ ገደማ የጨመረ ሲሆን በአራት ሳምንታት ውስጥ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል። ከግጭቱ ጋር ተያይዞ ነጋዴዎች በሚሰጡት ምላሽ ዓለም አቀፍ የጅምላ ገበያ ዋጋ ከቅርብ ወራት ወዲህ እየዋዠቀ ነው። አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት መጨረሻ በኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱ በኋላ ቴህራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ዘግታለች። ወሽመጡ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ነዳጅ ዘይት እና የተጣራ የተፈጥሮ ጋዝ የሚተላለፍበት ዋነኛ መስመር ነው። አሁን ላይ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗