" በእንቦጭ አረም ላይ ሲሰራ የነበረው የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ፈርሷል " - የአማራ ክልል የአካባቢ ባለስልጣን
" በእንቦጭ አረም ላይ ሲሰራ የነበረው የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ፈርሷል " - የአማራ ክልል የአካባቢ ባለስልጣን የጣና ሐይቅን እና በክልሉ የሚገኙ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን ከብክለት፣ ከአረም(እንደ እንቦጭ) ወረራ እና ከመጥፋት አደጋ ለመታደግ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 2004 ዓ.ም ተቋቁሞ የነበረው የጣና ሐይቅና ሌሎች የውኃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ መፍረሱን የክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። በክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የአረም ዝርያ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ተወካይ የሆኑት አቶ ድልነሳው ስመኘው " በኤጀንሲው ስር ይሰሩ የነበሩ ተግባራት በሙሉ በክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሰሩ ኤጀንሲው በክልሉ የመንግስት አደረጃጀት በአዋጅ እንዲፈርስ ተደርጓል " ብለዋል። አክለውም " በኤጀንሲው ስር የነበሩ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗