የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ

ADDIS_REPORTERneutral2026-07-15 04:36:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

የአዲስ አበባ ታክሲዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ክፍያ እንዲሰበስቡ ተወሰነ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የታክሲ አሽከርካሪዎች ከተወሰነው ታሪፍ በላይ እንዲሚያስከፍሉ ከማኅበረሰቡ የሚነሳውን ቅሬታ ለመፍታት ክፍያው ከመነሻው እንዲሰበሰብ የሚያስገድድ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አስታውቋል። አሽከርካሪዎች በታሪፍ መመሪያው መሠረት ብቻ ከመነሻው የትራንስፖርት ክፍያ እንዲሰበስቡ ለማስቻል ተቆጣጣሪዎች በመነሻ መጫኛ ቦታዎች ላይ ተመድበው ሥራ መጀመራቸውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተናግረዋል። ይህ አሠራር በጉዞ ወቅት "ሒሳብ ጨምሩ" በሚል ከአሽከርካሪዎች የሚነሳውን አግባብነት የሌለው ጥያቄ ለመግታት የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል። ይሁን እንጂ አዲሱ አሠራር ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ አንዳንድ ተግዳሮቶች መፈጠራቸውን የቢሮው ኃላፊዎች ጠቁመዋል። በከተማዋ በሚገኙ…

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]