የአውሮፓ ህብረት በሱዳን ወርቅ ላይ ማዕቀብ ጣለ
የአውሮፓ ህብረት በሱዳን ወርቅ ላይ ማዕቀብ ጣለ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት የሀገሪቱን የጦርነት ኢኮኖሚ ለማዳከም እና የቀጠለውን ግጭት የገንዘብ ምንጭ ለመቀነስ ከሱዳን የሚመጣን ወርቅ መግዛት፣ ማስገባት (ማስመጣት) ወይም ማጓጓዝ ላይ ነው ማዕቀብ የጣለው። ማዕቀቡ ከሱዳን የሚመጣን ወርቅ መግዛት፣ ወደ ሀገር ማስገባት ወይም ማጓጓዝ ላይ የተጣለ ሙሉ እገዳ ሲሆን ለወርቅ ማዕድን ማውጣት እና ማጣራት ሂደት ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውሉትን ሜርኩሪ እና ሲያናይድ ኬሚካሎችን ለሱዳን መሸጥ፣ ማቅረብ፣ ማስተላለፍ ወይም መላክ ይከለክላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከወርቅ እና ከእነዚህ ኬሚካሎች አቅርቦት ጋር የተያያዙ ቴክኒካዊ እገዛ፣ የፋይናንስ ድጋፍ ማድረግ ህብረቱ አግዷል፡፡ @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗