የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

FANATELEVISIONneutral2026-07-15 11:59:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት ልሂቃን በሚፈጥሩት ግጭት ሕዝባችን ቢታመስም ባህላችን ግን ለምክክር ያደላ ነበር። ቤታችን፣ ሞሰባችን፣ አቀማመጣችን፣ ማብሰያችን፣ ወዘተ ክብ ናቸው። ይሄውም ነገርን ሰብሰብ ብሎ በመመካከር ለመከወን እንዲያመች የተሠራ ነው። ክብ መነሻና መድረሻ የለውም። ሩቅና ቅርብ የለውም። ወጪና ገቢ የለውም። ሁሉንም በእኩልነት ያሳትፋል። ይሄንን የተረሳ ባህላችንን ወደ ሀገራዊ ምክክር አምጥተነዋል። ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን መጥተው በጋራ ይመክራሉ። እሺ በጄ ያለ ሁሉ ዕድል ተሰጥቶታል። እነሆ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያውያን ለነገ እንድትሆን ሆና ልትገነባ ተሰባስባለች። የሀገር ጸሎት ልብና ጆሮ ከእናንተ ጋራ ነው።

Read the full story at fanatelevision ↗
AdYour ad here[email protected]