" የእርስ በእርስ ጦርነት ከውጭ ጠላት ጋር ከሚደረግ ጦርነት የበለጠ ጎጂ ነው " - ኦባሳንጆ
" የእርስ በእርስ ጦርነት ከውጭ ጠላት ጋር ከሚደረግ ጦርነት የበለጠ ጎጂ ነው " - ኦባሳንጆ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና የአሁኑ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ በተካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገው ነበር። " በናይጀሪያ እና በኢትዮጵያ መካከል መመሳሰሎች አሉ " ያሉት ኦባሳንጆ " ይሄውም የእርስ በእርስ ቀውስ ችግር አለብን " ብለዋል። ኦባሳንጆ፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ከውጭ ጠላት ጋር ከሚደረግ ጦርነት የበለጠ ጎጂ መሆኑን በማንሳት፣ የናይጄሪያን የጦርነት ታሪክ በማስታወስ ለኢትዮጵያ ሀገራዊው የምክክር ሂደት ያለውን አስፈላጊነት አብራርተዋል። ሌላው በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ፣ የሰላምና የደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ በበኩላቸው፣ የሀገራዊ…
Read the full story at tikvahethiopia ↗