በአዲስ አበባ ከተማ አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የነበሩ 3ሺ አሽከርሪዎች በደንብ መተላለፍ ተቀጡ
በአዲስ አበባ ከተማ አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የነበሩ 3ሺ አሽከርሪዎች በደንብ መተላለፍ ተቀጡ የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት አልኮል ወይም አደንዛዥ እጽን ተጠቅሞ ማሽከርከርን ለመከላከል የቁጥጥር ስራ አከናውኗል። የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በተካሄደው የቁጥጥር ሥራ 3,356 አሽከርካሪዎች አልኮል ጠጥተው ሲያሽከረክሩ በመገኘታቸው በደንብ መተላለፍ ተቀጥተዋል። ባለስልጣኑ ጠጥቶ ማሽከርከር ለአሽከርካሪውም ሆነ ለሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ ቁጥጥሩን በከተማዋ በሚገኙ 11ኡም ክፍለ ከተሞች አካሂዷል፡፡ በቀጣይም አልኮል ጠጥቶ ማሽከርከርንና ሌሎች የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን ለመከላከል ቁጥጥሩ እንደሚጠናከር ባለስልጣኑ ገልፆ…
Read the full story at addis_reporter ↗