ለኳስ ሲባል ሚስቱን ከወንበር ጋር‼️
ለኳስ ሲባል ሚስቱን ከወንበር ጋር‼️ በዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ውስጥ አንድ የ64 ዓመት አዛውንት ያለምንም መረበሽ ኳስ ለማየት ሲል ሚስቱን አፏን ሸፍኖ ከወንበር ጋር አስሮ ለ45 ደቂቃ ያህል አስገድዶ በማስቀመጡ ክስ ተመሰረተበት። ሰውየው ሚስቱን አፏን ሸፍኖ ከወንበር ጋር አስሮ ጨዋታውን በቴሌቪዥን ሲመለከት እንደነበር በክሱ ላይ ቀርቧል። ሰውዬው ሚስቱ በግልጽ መንቀሳቀስ ወይም መናገር እንዳትችል አድርጓታል። በቀረበው መሠረት ይህ ክስተት የቤት ውስጥ ጥቃት፣ ሕገ-ወጥ እገዳ እና በጋብቻ ውስጥ ስለ ማስገደድ አጠቃቀም ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል። አንድ ሰው ከፍላጎቱ ውጭ እንዳይንቀሳቀስ ወይም እንዳይናገር መከልከል ህጉ አይፈቅድም። በዚህም ሰውዬው ጥፋቱን አምኖ ክስ ተመስርቶበታል። [አዩዘሀበሻ] ======================== ለትክክለኛ ወቅታዊ መረጃ ቻናላችንን join…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗