ተጨማሪ የነዳጅ መስመር ሊዘጋ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-15 20:13:57 UTC
AdYour ad here[email protected]

ተጨማሪ የነዳጅ መስመር ሊዘጋ እንደሚችል ኢራን አስጠነቀቀች። አሜሪካ በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተጨማሪ ድብደባ ካካሄደች በኋላ ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይና በቀጣናው የሚገኙ ተጨማሪ የነዳጅና የጋዝ መላኪያ መስመሮችን ሊዘጉ እንደሚችል አስጠነቀቀች። የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ በድሮኖች፣ በአየር እና በባሕር ኃይል በመታገዝ የኢራንን የባሕር መከላከያዎችና የክሩዝ ሚሳዔል ማከማቻዎች ላይ ድብደባ እንደፈጸመ ገልጿል። በሁለቱ ሀገራት መካከል ዳግም የተባባሰው ጦርነት በሆርሙዝ ሰርጥ የነዳጅ ንግድን በማስተጓጎል የዓለም የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አድርጓል። በሌላ በኩል፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወደ ድርድር ካልተመለሰች ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃቶች እንደሚከተሉ አስጠንቅቀዋል። ሃምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]