#Update
#Update በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ወረርሽኙ እጅግ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ አዳዲስ በበሽታው የመያዝ ሁኔታዎች “ምንጫቸው ካልታወቁ የሰው ለሰው ንክኪዎች” መሆኑን ነው የገለጸው። ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰ ገና ጥቂት ወራት ብቻ ቢቆጠሩም፣ እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በአምስት የኮንጎ ግዛቶች ውስጥ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና ከ700 በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አልፏል። ይህም በታሪክ የተመዘገበው ሶስተኛው ትልቁ የኢቦላ ወረርሽኝ ሆኗል ተብሏል። @TikvahethMagazine
Read the full story at tikvahethmagazine ↗