አርጀንቲና እንግሊዝን በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ አለፈች
አርጀንቲና እንግሊዝን በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ አለፈች አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም ዋንጫው የግማሽ ፍጻሜ መርሐ ግብር አርጀንቲና እንግሊዝን በማሸነፍ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች። እንግሊዝ በአንቶኒ ጎርደን ግብ እስከ 85ኛው ደቂቃ ድረስ 1 ለ ዐ እየመራች ብትቆይም አርጀንቲና በኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ላውታሮ ማርቲኔዝ ግቦች ጨዋታውን አሸንፋለች። ሊዮኔል ሜሲ ለሁለቱም ግቦች ኳስ አመቻችቶ በማቀበል ቁልፍ ተጫዋች መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል። አርጀንቲና በፍጻሜው ከስፔን ጋር ትፋለማለች፡፡
Read the full story at fanatelevision ↗