የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር በአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ዘግበዋል‼️

ESAT_TV1neutral2026-07-16 10:24:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር በአሜሪካ የጦር ሠፈሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ዘግበዋል‼️ አሜሪካ በወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ተጨማሪ ድብደባዎችን ስትፈጽም ኢራን በቀጣናው የሚገኙ ተጨማሪ የንግድ መስመሮችን እንደምትዘጋ አስጠነቀቀች። የኢራን አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ “ጠብ አጫሪነቷን” እስክታቆም ድረስ የሆርሙዝ ወሽመጥ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ ተናግሯል። አክሎም በቀጣናው የሚገኙ ተጨማሪ የነዳጅ እና ጋዝ መላኪያ መስመሮችን እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል። ማስጠንቀቂያው የተሰማው የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) ሌሊቱን ካካሄደው የሰባት ሰዓት ድብደባ ተከትሎ የድሮን፣ የአየር እና የባሕር ጥቃቶችን መፈጸሙ ካስታወቀ በኋላ ነው። ከቅርብ ቀናት ወዲህ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተቀሰቀሰው አዲስ ጦርነት ለዓለም ምጣኔ ሃብት ወሳኝ የሆነውን የባህር ወሽመጥ እንቅስቃሴ አልባ አድርጎታል።…

Read the full story at esat_tv1 ↗
AdYour ad here[email protected]