ከሙያ ኃላፊነት ባሻገር በተግባር የታየ የእናትነት ፍቅር
ከሙያ ኃላፊነት ባሻገር በተግባር የታየ የእናትነት ፍቅር በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የፈተና ጣቢያ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥ የጸጥታ ጥበቃ ግዳጇን እየተወጡ የሚገኙ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከኃላፊነታቸው ባሻገር የሰብአዊነት አርአያ ሆነው ተገኝተዋል። ኢንስፔክተር አልማዝ ተሾመ እና ረዳት ሳጅን ራቢያ አብደላ የተመደቡበትን የጸጥታና የፈተና ማስፈጸም የሙያ ግዴታቸውን በብቃት ከመወጣት ባለፈ፣ ፈተና ላይ ለነበሩ ወጣት እናቶች ረዳት በመሆን ተፈታኞቹ ያለስጋት ፈተናቸውን እንዲወስዱ አድርገዋል። ምስጋና ይገባችኋል፡፡ 👏👏 @tikvahuniversity
Read the full story at tikvahuniversity ↗