ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ተወያዩ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ተወያዩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች በማኅበራዊ ትስሰር ገጽ መልዕክታቸው፣ "ከርዕሰ መስተዳድሯ ጋር አንዳንድ ሥራዎችን በትብብር ለመስራት ፍሬያማ ውይይት አድርገናል" በለዋል:: በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው-ተኮር ሥራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ ለመለዋወጥ፣ ትብብራቸውን አጠናክረው በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውንም ጠቅሰዋል
Read the full story at ebcnewsnow ↗