"ኢትዮጵያ እየመከረች ባለችበት ወቅት መመረቃችን ተስፋችንን ያለመልመዋል" ተመራቂዎች
"ኢትዮጵያ እየመከረች ባለችበት ወቅት መመረቃችን ተስፋችንን ያለመልመዋል" ተመራቂዎች የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደረጃ 4 እና 5 በመደበኛ እና በማታ መረሐ ግብር ያሠለጠናቸውን ከ400 በላይ ሠልጣኞች አስመርቋል። ተመራቂ ሠልጣኞች በሠለጠኑበት ሙያ ሀገራቸውን እና ወገናቸውን ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በተመረቅንበት ወቅት ኢትዮጵያ መምከሯ የቀጣዩን ገዞ የተሳካ ያደርገዋል ያሉት ተመራቂዎቹ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ እየመከረች ባለችበት ወቅት መመረቃችን ተስፋችንን ያለመልመዋል ብለዋል። የወይዘሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ይመር ተመራቂዎች በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ያገኙትን ዕውቀት ተጠቅመው ለሀገራቸው የመፍትሔ አካል መኾን እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የቤተሰብ፣ የመምህራን እና የሠልጣኞች…
Read the full story at amharamassmedia ↗