#ጥቆማ

TIKVAHUNIVERSITYneutral2026-07-18 19:05:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

#ጥቆማ አዲስ ሠልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክ አካዳሚ አሳውቋል። በኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ESL) ስር የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ፣ አዳዲስ ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን የትምህርት እና የመሠረተ ልማት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል። አካዳሚው ዘመናዊ የማስተማሪያ መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ካሪኩለሞች እና ብቁ የማስተማር አቅም በማሟላት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆኑን የአካዳሚው ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ገልፀዋል። ሲሙሌተሮች በመጠቀም እና በባቦጋያ ሐይቅ ላይ በሚካሄዱ የተግባር ስልጠናዎች በከፍተኛ የደህንነት እና የጥራት ደረጃ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ጠቁመዋል። አካዳሚው ከመሠረታዊ የባህር ላይ ደህንነት ስልጠናዎች ጀምሮ እስከ የመርከብ መኮንንነት…

Read the full story at tikvahuniversity ↗
AdYour ad here[email protected]