አሳዛኝ አደጋ:- የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼️
አሳዛኝ አደጋ:- የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼️ በሶማሌ ክልል ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፣ በ3 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሷል። አደጋው የተከሰተው በአንድ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና በአይሱዙ ጭነት መኪና መካከል በተፈጠረ ግጭት መሆኑን የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አስታውቋል። የአደጋው መንስኤ በአሁኑ ወቅት በፖሊስ እየተጣራ ይገኛል። የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሐመድ በአደጋው ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን የገለጹ ሲሆን፣ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናት ተመኝተዋል። @Addis_Reporter @Addis_Reporter
Read the full story at addis_reporter ↗