ራሷን በሽጉጥ አጠፋች ተባለ‼

WASULIFEneutral2026-07-19 16:05:03 UTC
AdYour ad here[email protected]

ራሷን በሽጉጥ አጠፋች ተባለ‼ በትግራይ ክልል ዕዳጋ ዓርቢ ከተማ በጀግንነቷ የምትታወቀው ወጣቷ እናት ታጋይ ብርኽቲ ተኽላይ፣ መኖሪያ ቤቷን ዘግታ በራሷ ሽጉጥ ህይወቷን ማጥፋቷ ታውቋል። ምንም እንኳን ህይወቷን ለማትረፍ ወዲያውኑ ወደ አክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ተወስዳ የነበረ ቢሆንም፣ በህክምና እርዳታ ህይወቷን ማዳን ሳይቻል ቀርቷል። በዚህ ዓመት ትዳር መስርታ ገና የጨቅላ ህጻን እናት የነበረችው የዚች ወጣት አሳዛኝ ህልፈት በቤተሰብና በወዳጅ ዘመዶቿ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሃዘንን ፈጥሯል። የታጋይ ብርኽቲ ተኽላይ የቀብር ሥርዓት ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በትኹል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እመኛለሁ #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]