በቀብሪበያህ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎችን ሕይወት አለፈ

ZENA24NOWneutral2026-07-19 16:35:03 UTC
AdYour ad here[email protected]

በቀብሪበያህ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ12 ሰዎችን ሕይወት አለፈ በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በተከሰተ ከባድ የመኪና አደጋ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል። አደጋው ሊከሰት የቻለው ዛሬ ረፋድ ሶስት ሰዓት ላይ አንድ የአይሱዚ መኪና «ፎርስ» ተብሎ ከሚጠራ ሌላ ተሽከርካሪ ጋር በድንገት በመጋጨቱ ሲሆን በዚሁ አሳዛኝ አጋጣሚ የ12 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል። በተጨማሪም በአደጋው ሦስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።በአሁኑ ወቅት የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ አደጋው በትክክል በምን ምክንያት ሊከሰት እንደቻለ ለማወቅ በአደጋው ቦታ ላይ ጥብቅ ምርመራ እያደረገ ይገኛል። #ዳጉ_ጆርናል

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]