#Update

ADDIS_NEWSneutral2026-07-20 09:10:42 UTC
AdYour ad here[email protected]

#Update በሶማሊ ክልል በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ 12 ሰዎችን ለመቅበር የሄዱ ሶስት ሰዎች በአፈር መደርመስ ህይወታቸው አለፈ በሶማሊ ክልል ፋፈን ዞን ቀብሪበያህ ወረዳ ጉዮው ቀበሌ በተከሰተ ከባድ የመኪና አደጋ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። አደጋው ሊከሰት የቻለው እሁድ ረፋድ ሶስት ሰዓት ላይ አንድ የአይሱዚ መኪና «ፎርስ» ተብሎ ከሚጠራ ሌላ ተሽከርካሪ ጋር በድንገት በመጋጨቱ ሲሆን በዚሁ አሳዛኝ አጋጣሚ የ12 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል። በተጨማሪም በአደጋው ሦስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።የደረሰውን የትራፊክ አደጋ ተከትሎ በቀብር ላይ በነበሩ ወገኖች ላይ የመቃብር ቦታ አፈር ተደርምሶ ተጨማሪ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ10 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ገልጿል ። ቢሮዉ…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]