ባለቤት አልባ ውሾች የደህንነት ስጋት አሳድረውብናል ሲሉ የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ገለፁ
ባለቤት አልባ ውሾች የደህንነት ስጋት አሳድረውብናል ሲሉ የኮዬ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ገለፁ በኮዬ ፈጬ 17 ሳይት ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ከብሎክ 462 እስከ 472 ባለው ክልል የሚኖሩ ነዋሪዎች በውሾች መበራከት ሳቢያ ለከፍተኛ ስጋት መዳረጋቸውን ገልጸዋል። በጋራ መኖሪያ ቤት አስተዳደር ህግ መሠረት በኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ ውሾችን ማሳደግና ማኖር የተከለከለ ቢሆንም ቁጥራቸው ከ5 በላይ የሆኑ ባለቤት አልባ ውሾች በአካባቢያቸው በነጻነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል። እነዚህ ውሾች በተለይም ለህጻናት ደህንነት ከፍተኛ ስጋት መሆናቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ ልጆቻችን ትምህርት ቤት በሚሄዱበትና በግቢ ውስጥ በሚጫወቱበት ወቅት በውሾቹ ከመደናገጣቸው ባለፈ ለንክሻ እየተዳረጉ ይገኛሉ" ብለዋል። ችግሩ ከህጻናት አልፎ ስራ አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው…
Read the full story at zena24now ↗