🇺🇸 አሜሪካ በአርሲ የተፈጸመውን የሲቪሎች ግድያ አወገዘች። መንግሥት ጥቃት የፈጸሙትን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቃለች።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-10-31 19:17:02 UTC
AdYour ad here[email protected]

🇺🇸 አሜሪካ በአርሲ የተፈጸመውን የሲቪሎች ግድያ አወገዘች። መንግሥት ጥቃት የፈጸሙትን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቃለች። በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን ሲቪሎችን በዒላማ ያደረገ ግድያ እንደተፈጸመ የወጡ ሪፖርቶች እንዳሳሰቧቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ ገለጹ። አምባሳደሩ አሜሪካ በሃይማኖት ፣ በብሔር ወይም በፖለቲካ ምክንያት የሚፈጸም ጥቃትን እንደምታወግዝ ጠቅሰው፣ በማንኛውም ቡድን ላይ የሚፈጸሙ እንዲህ ያሉ አስከፊ ጥቃቶች መቆም እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን እንዲያጣራና ጥቃቱን የፈጸሙ አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብም ጥሪ ማቅረቧን አምባሳደሩ ገልጸዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥቅምት 21 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]