​ደቡብ ሱዳን የነጻ ቪዛ መብት ለግብፅ እና ለታንዛኒያ ዜጎች ብቻ ሰጥታለች።

TIKVAHETHMAGAZINEneutral2026-07-20 10:31:36 UTC
AdYour ad here[email protected]

​ደቡብ ሱዳን የነጻ ቪዛ መብት ለግብፅ እና ለታንዛኒያ ዜጎች ብቻ ሰጥታለች። የደቡብ ሱዳን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት፣ ከግብፅ እና ከታንዛኒያ ዜጎች ውጭ የሌሎች ማናቸውም የዓለም አገራት ዜጎች ወደ አገሪቱ ለመግባት ለቪዛ ተገቢውን ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው አስታውቋል። በአዲሱ የአገልግሎት ክፍያ መዋቅር መሠረት የአብዛኞቹ የዓለም አገራት ዜጎች ለአንድ ጊዜ መግቢያ 100 ዶላር፣ ለሶስት ወራት በተደጋጋሚ መግቢያ 200 ዶላር፣ እንዲሁም ለስድስት ወራት በተደጋጋሚ መግቢያ 350 ዶላር መክፈል ይኖርባቸዋል ተብሏል። በሌላ በኩል ደግሞ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የኬንያ እና የኡጋንዳ ዜጎች ከተቀሩት የዓለም አገራት በተለየ ሁኔታ አነስተኛ የቪዛ ክፍያ እንዲከፍሉ ተወስኗል። በዚህም መሠረት የእነዚህ አገራት ዜጎች ለአንድ ጊዜ መግቢያ 50 ዶላር፣…

Read the full story at tikvahethmagazine ↗
AdYour ad here[email protected]