" ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የከፈልንበትን አፓርታማዎቻችንን አስረክበን" በሚል ስድስት ቤት ገዢዎች ኖህ ሪልስቴትን ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስደውታል።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-07-20 11:27:21 UTC
AdYour ad here[email protected]

" ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የከፈልንበትን አፓርታማዎቻችንን አስረክበን" በሚል ስድስት ቤት ገዢዎች ኖህ ሪልስቴትን ወደ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወስደውታል። ገዢዎቹ ክስ የመሰረቱበት በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ሴቶች አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ባለ19 ወለል ኖህ ቪክትሪ ሳይት ነው። ከሳሾቹ እንደገለጹት፣ አልሚው ኖህ ሪልስቴት በ36 ወራት ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ አፓርታማዎቹን ሊያስረክብ በውል ቢገባም፣ በተግባር ግን ስድስት ዓመታት እንደፈጀበት ገልጸዋል። ከሳሾቹ እንደሚሉት፣ ኖህ ሪልስቴት የአፓርትመንት መኖሪያ ቤቶቹን ከውሉ ቀን ጀምሮ በሦስት ዓመታት ውስጥ አጠናቆ ሊያስረክባቸው ውል ቢገባም፣ "በዚህ ጊዜ ውስጥ ተከሳሽ ለከሳሾች አፓርትመንቱን አጠናቆ ማስረከብ አልቻለም" ብለዋል። ግንባታው የተጠናቀቀው በዚህ ዓመት ከሦስት ወራት በፊት መሆኑን ጠቅሰው፣…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]