የድሬዳዋ አስተዳደር ዕውቅና በሌላቸው የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ እገዳ ጣለ
የድሬዳዋ አስተዳደር ዕውቅና በሌላቸው የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ እገዳ ጣለ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከአስተዳደሩ ዕውቅናና ሕጋዊ ፈቃድ ውጪ የሚዘጋጁ የሙዚቃ ድግሶችና የትኬት ሽያጮች በጥብቅ የተከለከሉ ናቸው ሲል አስታውቋል። በተለይም መጪው ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም /July 25, 2026 ሊካሄድ ታቅዶ የትኬት ሽያጭ እየተከናወነበት የሚገኘውን የኮንሰርት ዝግጅት በመጥቀስም ህብረተሰቡ ራሱን ከገንዘብና ከጊዜ ኪሳራ እንዲጠብቅ ሲል ነው የገለጸው። አስተዳደሩ በዚህ ሕገ-ወጥ ተግባር ላይ የተሰማሩ አዘጋጆችም ሆኑ ለዝግጅቱ ቦታ የሚያከራዩ አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰበ ሲሆን፣ መመሪያውን ተላልፎ በሚገኝ በማንኛውም አካል ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል @TikvahethMagazine
Read the full story at tikvahethmagazine ↗