ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ታጥረው የተተዉ መሬቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ታጥረው ያለምንም አገልግሎት የተቀመጡ መሬቶችን በማጣራት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል። ከንቲባዋ ይህን ያስታወቁት፣ በከተማ አስተዳደሩ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ ማጠቃለያ መድረክ ላይ ነው። እንደ ከንቲባዋ ገለጻ፣ አዲስ አበባ መሬት ታጥሮ የሚቀመጥባት ከተማ መሆን እንደሌለባት ቀደም ሲል የተደረሰውን ስምምነት የሚጥሱ አካላት ተጨማሪ ዕድል እንደማይሰጣቸው አስጠንቅቀዋል። በሌላ በኩል፣ በከተማዋ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑን በመግለጽ፣ በርካታ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶች ያለ የደህንነት ችግር በሰላም መጠናቀቃቸውን አስታውሰዋል።…
Read the full story at addis_reporter ↗