በሀዋሳ ከተማ 120 ሊትር ነዳጅ የሚይዝ ህገ-ወጥ ታንከር በባጃጁ ላይ አስገጥሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሹፌር ተያዘ
በሀዋሳ ከተማ 120 ሊትር ነዳጅ የሚይዝ ህገ-ወጥ ታንከር በባጃጁ ላይ አስገጥሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሹፌር ተያዘ በሀዋሳ ከተማ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪ ላይ ህገ-ወጥ ተጨማሪ ታንከር በመግጠም ነዳጅ ሲቀዳ የነበረው ሹፌር በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።ግለሰቡ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪ ውስጥ የወንበር ቅርጽ ያለው ህገ-ወጥ ታንከር አስገጥሞ መገኘቱ ተገልጿል። የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምክትል አዛዥና የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አብስራ አመሎ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ግለሰቡ በተሰራው ህገ-ወጥ ታንከር ውስጥ 120 ሊትር ነዳጅ የተገኘ ሲሆን ባጃጁ በመደበኛ ሁኔታ መያዝ የሚችለው 8 ሊትር ብቻ ነዉ። በዚህም የባጃጅ ሹፌሩን ጨምሮ በጋራ ሲሰሩ የነበሩ የነዳጅ ማደያው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር…
Read the full story at zena24now ↗