የኬንያ መንግሥት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊሸፍን ነው፡፡
የኬንያ መንግሥት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎችን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊሸፍን ነው፡፡ የብሔራዊ ፈተና ወስደው የሚያልፉና በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች የሚመደቡ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት ክፍያ በመንግሥት የሚሸፈን መሆኑን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊያም ሩቶ አሳውቀዋል፡፡ አዲሱ መመሪያ በሀገሪቱ የሕግ አውጪ አካላት ከፀደቀ በኋላ ከመጪው መስከረም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡ ይህም የተማሪዎችን (ወላጆች) የፋይናንስ ፍላጎት በመገምገም የመንግሥት ድጋፍ ይሰጥበት የነበረውን የከፍተኛ ትምህርት የፋይናንስ ማዕቀፍ የሚቀይር ይሆናል፡፡ አዲሱ ማዕቀፍ ወላጆች በፈቃደኝነት ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት የክፍያ ጫና እንዳይኖርባቸው የሚያደርግና ድህነት ትምህርት እንዳያስተጓጉል የሚያስችል ነው ተብሏል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የጥራት ክፍተት ሳይፈጥሩ ከፍተኛ ቁጥር…
Read the full story at tikvahuniversity ↗