በአማራ ክልል በቀሪ 8 ምርጫ ክልሎች ምርጫ ሊካሄድ ነው።
በአማራ ክልል በቀሪ 8 ምርጫ ክልሎች ምርጫ ሊካሄድ ነው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ተኛውን ዙር ቀሪ ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል በስምንት ምርጫ ክልሎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ለዚህ ሥራም ለመራጮች ምዝገባ እና ለድምፅ መስጫው ዕለት በሁሉም ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎችን በጊዜያዊነት ለመቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል። አመልካቾች ተከታዩን ማስፈንጠሪያ https://nebe-election.org/recruitment እንዲጠቀሙ የተገለጸ ሲሆን ከዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት እንደሚቆይ ቦርዱ አስታውቋል። ከዚህ ቀደም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ የተሳተፉ ምርጫ አስፈጻሚዎች ከክፍያ ጋር ተያይዞ ሰፊ ቅሬታ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል። @TikvahethMagazine
Read the full story at tikvahethmagazine ↗