በትግራይ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ቀጠፈ
በትግራይ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ቀጠፈ በትግራይ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱ ተቃራኒ የአየር ሁኔታዎች በሕዝብና በግብርና ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆናቸው ተገልጿል። በአንድ በኩል በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ በአዝርእትና በመስኖ ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል። በሌላ በኩል ደግሞ 176 የቀበሌ ገበሬ ማህበራት እስካሁን የክረምት ዝናብ እንዳላገኙ ተገልጿል። በማዕከላዊ ዞን ወረዳ ቀይሕ ተኽሊ ዶክተር አታኽልቲ ቀበሌ ገበሬ ማህበር፣ ለሁለት ሰዓታት ያለማቋረጥ የዘነበው በረዶ አዘል ከባድ ዝናብ የአንድ ሕፃንን ሕይወት ከመቅጠፉ በተጨማሪ በአዝርእትና በመስኖ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል። በተመሳሳይ በዞኑ ወረዳ አሕፈሮም ሴሮ ቀበሌ የዘነበው ብርቱ ዝናብም በአዝርእትና በአትክልት ላይ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው…
Read the full story at zena24now ↗