በትግራይ ክልል የተከሰተ የከፋ የአየር ሁኔታ የሕይወትና የንብረት ጉዳት አድረሰ

BROOK_NEWS_ETHIOPIAneutral2026-07-22 16:33:13 UTC
AdYour ad here[email protected]

በትግራይ ክልል የተከሰተ የከፋ የአየር ሁኔታ የሕይወትና የንብረት ጉዳት አድረሰ በማዕከላዊ ዞን ቀይሕ ተኽሊ እና አሕፈሮም ወረዳዎች በጣለው ከባድ በረዶ አዘል ዝናብ የአንድ ሕፃን ሕይወት ያለፈ ሲሆን በአዝእርት፣ በመስኖ እና በአትክልት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ወድቋል። በሌላ በኩል ደግሞ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ጥበቃ ቢሮ እንደገለጸው፣ በክልሉ ከሚገኙ 600 ቀበሌዎች ውስጥ 176 ቀበሌዎች እስካሁን ምንም ዓይነት የክረምት ዝናብ አላገኙም። ​ በአንዳንድ አካባቢዎች የጣለው ከመጠን ያለፈ ዝናብ ጉዳት እያደረሰ ባለበት ሁኔታ፣ በሌሎች አካባቢዎች ያለው የዝናብ እጥረት በእርሻና በምርት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ

Read the full story at brook_news_ethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]