በጅጅጋ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼
በጅጅጋ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼ በሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ ካራማራ ክፍለ-ከተማ (10ኛ ሰፈር) ማምሻውን በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ሕይወታቸው ካለፉት መካከል አምስቱ ወንዶችና ሁለቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ አደጋውን ያደረሰው «ሲኖትራክ» የጭነት ተሽከርካሪ እንደሆነ ተገልጿል። በአደጋው ጉዳት የደረሰበት አንድ ሕፃን ወደ ህክምና ተቋም ተወስዶ አስቸኳይ እርዳታ እየተደረገለት ይገኛል።ፖሊስ የአደጋውን መንስኤና የጉዳቱን መጠን ለማወቅ ሰፊ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል። ከሰሞኑ በክልሉ ቀብሪበያህ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 12 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…
Read the full story at wasulife ↗